ጸጋ መጽሐፍት ቤትን ይጎብኙ

ጸጋ መጽሐፍት ቤትን ይጎብኙ

በቅርብ የወጡ መንፈሳዊና ጥናታዊ መጻሕፍትን ለመላው ሰሜን አሜሪካ አናቀርባለን:: በቀላሉ ከ  http://shop.tsega.com/Books ላይ ይዘዙን::

 

ስተያየት በመጽሓፍ ላይ:

በቅርቡ ባላሳትመውም፣ ውሎ አድሮ ለንባብ የማበቃው፣ መጽሐፍ አለኝ። መጠሪያው ተሳስቼ ነበር የሚል ነው። የዚህን ዝግጅት አንጓ መልእክት ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት በማቴቴስ መጽሔት ላይ ቤተ ክርስቲያንን መትከል ወይስ መክፈት በሚል ርእሰ ነገር ላይ “ተሳስቼ ነበር” ብዬ መጻፌን አልዘነጋውም። ይህንንም ያደረግሁት በአደባባይ ለተገለጠ ስሕተት የአደባባይ ምልሽ በመስጠት ማረም ግድ መኾኑን በማመን ነበር።

ዘንድሮ ደግሞ ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን የደነበረው በቅሎ በሚል [ርእስ] የአስተምህሮ ልጓም አስፈላጊ መኾኑን ሊያሳውቀን ተነሥቷል። መጽሐፉ ምጥን ገጾች ያሉት ቢኾንም፣ የእርጋታ ንባብን ይሻል። ግራ ቀኙን በማጤን፣ ለካስ እንደ ቤርያ ሰዎች ካልኾንን፣ ወየውልን ያሰኛል። መጽሐፉ ራሳችንን አካትተን ሁሉን እንድንፈትሽ ግድ ይለናል። ፍተሻው ተሳስቻለሁ፣ ተሳስተናል ወይም አስተውናል በማሰኘት ከከንቱ ሩጫችን ይገታናል።

በርግጠኛነት ዛሬ ብዙ ምእመን፣ ብዙ ሰባኪ፣ ብዙ መጋቢ፣ ብዙ ዘማሪ በሀገሪቱ እየተርመሰመሰ ነው። አብዛኛው በዕለታዊ ኑሮ “ጠበል ፈለቀ”በተባለበት ስፍራ ፈጥኖ በመድረስ ያገኘውን እየሸመተ ነው። ይሕ ዐይነት ሸመታ ደግሞ ጕዳትን ያስከትላል። የደነበረው በቅሎ ይህን ሊያሳየን ተጻፈ። እንኪያስ የክርስቶስ ነኝ ያለ ሁሉ ዘመኑ ሳያልፍ ከወዲሁ እንዲጠነቀቅ ጥሪ ቀርቦለታል።

ሰሎሞን፣ በመጋቢነት ጸጋውና ጥሪው በ የትሩፋን ናፍቆት መጽሐፉ የመከረንን ምክር አሳድጎ፣ ዛሬም ሁሉን በመመርመር ፍሬያማ ኑሮን በቃሉ መሠረት እንመዝንም እንኖርበትም ዘንድ ሁላችንን ይጋብዛል።

የስሜ ታደሰ (መጋቢ) መጽሓፍት በ ጸጋ  ይገኛሉ
የኢትዮጵያ ባይብል ባፕቲስት ቸርች ፌሎሺፕ ፕሬዚዳንት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *