አዳምና ሔዋን መጽሔት

adamnahADD

አዳምና ሔዋን መጽሔት በትንሣኤ አንድ ብላ ስትመጣ መነሻ ያደረገችው ጋብቻን ከስሩ መንግሎ በሚጥለው የፍቺ ችግር ላይ በማተኮር ነው። ፍቺ የቤተክርስቲያን ብሎም የአገር አሳሳቢ ችግር እየሆነ መምጣቱን አካባቢያችንን በማየት ብቻ መናገር እንችላለን። ከጥቂት አመታት በፊት ይሰራበት በነበረው አንድ ክርስቲያናዊ አገልግሎት ውስጥ ስድስት ጥንዶች እንደነበሩ እና ከነዚያ ጥንዶች መካከል ሶስቱ ጥንዶች ትዳራቸው በፍቺ እንደተጠናቀቀ ሲናገር የሰማነውን አንድ ሰው አካባቢያችንን እንድናይ ጠቁሞን እኛም በልቦናችን ፈትሸን መታዘብ ችለናል።

የቤተሰብ ምስረታ በጋብቻ ላይ ተጥሎ ሳለ ፍቺ ለምን በረከተ?ፍቺ ጣጣው እስከምን ድረስ ይዘልቃል? አዳምና ሔዋን ትኩረት የሰጠችው ጉዳይ ነው። ከሽፋን ስዕሉ ጀምሮ የፍቺን ኪሳራ ለማሳየት ሞክረናል።ጥንዶች ሲለያዩ የቀድሞ አካላቸው ተበላሽቶ ነው። ሴቲቱም የቀድሞ ባልዋ ስያሜም ሆነ ማንነት አብሯት ይቀራልና ቀሪው ዘመንዋ ፈተና የበዛበት ነው የሚሆነው። ወንዱም /ባል/ የተወሰነው የአካሉ ክፍል ከሚስቱ ጋር ሄድዋልና ጎድሎነት የሚሰማው ነው የሚሆነው። ብዙ ይናገራል የሽፋን ስዕሉ። አንባቢም የበኩሉን ሃሳብ ያነሳለታል። ገና ከጅማሬዋ ኮስተር ብላ የመጣች ብትመስልም የፍቅር ነውና አዳምና ሔዋንን በደስታ ተቀበልዋት።

መጽሔቷን ከእንቅልፏ እንድትነቃ የቀሰቀስዋትን ውድ ወገኖቻችንን በአንባብያንና በዝግጅት ክፍሉ ስም ማመስገን እንወዳለን።

 

Available for online subscription and paper version delivery in North America and Europe.

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *