ስነ ግጥም

ስነ ግጥም

ሰው የሆነ ለሰው – ፓ/ር ስንቱ ከሐረር

አንዳንድ ቀን አለ ልብን የሚሰብር
አንዳንድ ቀን አለ ለብቻ የሚያስቀር፤
ቢሆንም ግድ የለም ሁሉ ኋላ ዞሮ
ብቻነት ከፍ ሲል ሲበረታ ከሮ
ልብ ሰው ሲጠማ ነገር የሚጋራ
ጨለማን የሚያርቅ ተስፋን የሚያበራ፡፡
ነገር ግን ባይገኝ በመከራ መሃል
እኔ አለሁኝ ብሎ ጭንቅን የሚካፈል፤
አለ ሰውን ብሎ ስጋን የለበሰ
ሰው ለተራበ ልብ ፈጥኖ የደረሰ፡፡

ጥቂትም እረፉ – ሂሩት ደስአለኝ(ወ/ዊ)

በመውጣት በመውረድ
እንዲያው በመዋደድ
ሲጀመር ጀምሮ
ያላችሁ ከድሮ
ብዙ የደከማችሁ በመቀመጣችሁ
ነወር ለማለትም ብድግ ያላላችሁ
ብትነሱ መውደቅ ሞት የሚመስላችሁ
በጀልባ ተኝቶ ጌታም አረፍ ብሏል
ባሪያውም ከጌታው እንዳይበልጥ ተናግሯል
መሆኑን ብናውቅም እስከሞት ጥሪያችሁ
የጥሞና ጊዜ ትንሽ ከሌላችሁ
ሥጋ ደካማ ነው እንዳታንቀላፉ
ፈቀቅም በሉና ጥቂትም እረፉ

የማን እጆች ናቸው? – ሂሩት ደስአለኝ(ወ/ዊ)

ያለፉ ዓመታቴን
የኔን ጓዳ ጎድጓዳዬን
ውስጠ ህሊናዬን
እየቆሰቆሱ ስብከቴን ፀሎቴን
ህይወት ምልልሴን
ቆሻሻ እንዳፀዳ
ንጹህ እንዲቀዳ
በጥበብ የነኩ የልቤን ውስጥ ጓዳ
የማን ጥበበኞች?
የማንስ ጣት ናቸው ?
ዘመኔን በጥበብ ሊሞሉ በፍሬ
ቅጠል እየበላሁ ቅጠል አገልድሜ
ጎትተው ያወጡኝ ከኖርኩት አለሜ
የማን እጆች ናቸው?
ጥበቴን አስፍተው
አጥልቀው ቆፍረው
ሐቅን የሞሉብኝ የማንስ ጣት ናቸው?
ወለላ … ጎምዛዛ
ያጠጡኝ በአንድ ዋንጫ
በልቤ ፅላት ላይ
እውቀት ማለት እውነት
እውነት ማለት ቃሉ
ድርብ ትርጉም አለው
ሌላ ገጹን እይው
ብለው ያተሙብኝ
የማንም የማንም የማንም አይደሉ
ከአይኖቼ ዛጎል ምሰሶ የሰበሩ
ህይወቴን በቅጡ አፍርሰው የሠሩ
ያ’ምላክ ጣቶች ናቸው ጥበብ የተካኑ

sintayehu demekech Belaynesh

 

 

 

 

 

 

 


 

Zelealem Mengistu – Ezra

አትፍራው ንገረው
ንገረው አትፍራው
ክፉ እንደሆን ሥራው
ማመሰቃቀሉን ቀኙን ወደ ግራው
የአምላኩን ኪዳን
እርግፍ አርጎ ትቶ
ከፍለጋው ርቆ
ከመንገዱ ስቶ
ሰውን እያሳተ መሆኑን ንገረው
ፀሐይዋ ጠልቃበት መከራ ሳይመክረው
ጠል መከልከሉ፥
ሰማይ መዘጋቱ፥
ውኃው መመጠጡ፥
ምድር መገርጣቱ፥
አትፍራው ንገረው
እርሱ እንደሁ ምክንያቱ፤
አትፍራት ንገራት
ምክንያቱ እርሷም ናት
ያገሯን አማልክት
የወንዟን አጋንንት
ይህች ክፉ አታላይ
ጭና በጀርባው ላይ
ባሏን እንደ ጌኛ ለጉማ የነዳችው
የጌታን ነቢያት አሳዳ የፈጀችው
እርሷ ናት
ንገራት።
እጥፍ ድርብ ሆኖ
ዋጋ ተተምኖ
ትከፍያለሽ በላት።

ezraPoem 2 ezraPoem


 

 

 

 

 

 

 

 


 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *