ቀንዲል – ነፃ መጽሔት

ቀንዲል – ነፃ መጽሔት

እንደ መንደርደሪያ

ጥንት ግሪኮች በመዲናቸው አቴንስ ከሰሯቸው ጣዖታት መካከል የማይታወቀው አምላክ ወይንም በጽርሁ “አግኖስቶስ ቲዮስ” ተብሎ የሚጠራው ጣዖት አንዱ ነው፡፡“አግኖስቶስ ቲዮስ” ከመመለኩ በፊት የግሪክ ሰዎች ሰበብ አስባብ ፈልገው የሚያመልኳቸው የትልቁ ዚዮስ ምንዝር አማልክት ብዙ ናቸው፡፡ነገር ግን የታመኑባቸው እነዚህ አማልክት በአንድ ወቅት የሀገሬው ህዝብ ከገጠመው ድርቅና በሽታ መዳን ተስኗቸው ድርቁና በሽታው በርትቶ ሰዎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ሲገድል ነገር ዓለማቸው ተመሰቃቀለ፤ ግራተጋቡ፡፡ጥቂት አልቆዩም ይህ ድርቅና በሽታ እንዳይደገም ልናመልከው እየተገባንና ሳናመልክ ለዘነጋነው ደግም ተበሳጭቶ ለቀጣን አምላክ ምስጋናና ውዳሴ እናቅርብለት በሚል የማይታወቅ አምላክ ወይንም “አግኖስቶስ ቲዮስ” የሚል መጠሪያ ያለው ጣዖት ሰሩ፡፡ስለዚህም የጥንት ግሪኮች ይህ ጣዖት የቀድሞው ድርቅና በሽታ በግሪክ ምድር ዳግም እንዳይከሰት ይከላከላል በሚል እምነት ያመልኩት ጀመር፡፡

ሀገሬን፣ አዎ አትዮጵያዬን፣ ይሻርልህ አዎ እናት ሀገሬን አንዴ በ66፣ በ77፣ በ86፣ በ88፣ሌላ ጊዜ በ92፣ አልበቃ ሲለው በ2000 ሄድ መጣ እያለ አሁን ደግሞ በ2007 በሶማሊያ፣በአፋር፣በማዕከላዊና በምስራቃዊ የኦሮሚያ ክልል (አርሲና ቦረና) በተለይ ደግሞ በወሎ እየተመላለሰ ስለሚወተውተን ድርቁ ስጽፍ መቼም ቅሉ እንደግሪኮቹ “አግኖስቶስቲዮስ” የሚል ጣዖት ሰርተን እግዚዖ እንድንል አይደለም፡፡ይልቁንም ከዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ለመውጣት ከተለያየ አንጻር የሚቀርቡ ትንታኔዎችን በመመልክት የችግሩን መንስኤና መፍትሄ በትክክል ወደሚያስገነዝበን መጽሀፍ ቅዱሳዊው ምልከታ አምርቶ የጋራ አቋም ለመያዝ ነው፡፡ስለዚህም በዚህ ጽሁፍ ስለድርቅ መንስኤና መፍትሄ የሚሰጡ ትንታኔዎችን አቀርባለሁ፤አብራችሁኝ ዝለቁ፡፡ምንድን ነው እየሆነ ያለው?

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *