እንዴት አውቃለሁ? ኮነ ፍስሐ -Tsega.com

እንዴት አውቃለሁ? ኮነ ፍስሐ -Tsega.com

ከእግዚአብሔር ጋር ያለን መንፈሳዊ መቀራረብ የሚያድገው ቀስ በቀስ፣ ደረጃ በደረጃ አይደለም፣ ለዚህም ሁለት ምርጫ ብቻ ነው የሚኖረን፦ መጀመርያውኑ ይህ መንፈሳዊ መቀራረብ አለን ወይም የለንም። እግዚአብሔር ከሃጥአት የሚያነጻን ደረጃ በደረጃ አይደለም። ከዛሬ ይልቅ ነገ በበለጠ ሁኔታ ከሃጢአት አያነጻንም። “በብርሃን ብንመላለስ” አሁኑኑ “ከሃጢአት ሁሉ” ነጽተናል ማለት ነው(1  ዮሓ 1:7)። ጉዳዩ የመታዘዝ ወይም ያለመታዘዝ ነው፥ ከታዘዝን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ወይም መቀራረብ ወድያውኑ ፍጹም ይሆናል። ካልታዘዝን ደግሞ የጨለማና የሞት ጥላ ያጠላብናል።

እግዚአብሔር የገለጻቸው እውነቶች ሁሉ በመታዘዝ እስኪገለጡ ድረስ ድፍን ነገሮች ናቸው። መንፈሳዊ እውነት የሚበራልን በፍልስፍና ወይም በአስተሳሰብ ምጥቀት አይደለም። ስለዚህም መንፈሳዊ እውነት በውስጥህ እንዲሰራ ፍቀድለት እንጂ አትጨነቅ። የእግዚአብሔርን እውነት ማወቅ  የምትችልበት መንገድ የራስህን ጥረት ፍለጋ ትተህ ዳግም ስትወለድ ብቻ ነው። በመጀመርያ ለተገለጸልህ ነገር ከታዘዝህ እግዚአብሔር የሚቀጥለውን እውነት ይገልጽልሃል። ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ የተጻፉ ብዙ መጽሐፍትን ማንበብ ትችል ይሆናል፣ ለአምስት ደቂቃ  ያለማወላወል ብትታዘዝ ግን ለዘመናት ፈልገህ ያጣኀው እውነት የጠራራ ፀሃይ ያህል ይበራልሃል።

ለትልቁ ለትንሹ “ ይህ ነገር አንድ ቀን ግልጽ ይሆንልኝ ይሆናል” አትበል፥ ምክንያቱም አሁኑኑ ልትረዳው፣ አሁኑኑ ግልጽ ሊሆንልህ ይችላል።  ይህን መረዳት የምታገኘው በማያቁዋርጥ ጥናት ሳይሆን በመታዘዝ ነው። አንዲት ትንሽ ናት የምትላት መታዘዝ ሰማይን መክፈት ትችላለች፣ የጠለቀ የእግዚአብሔርንም እውነት ትገልጣለች። ይሁን እንጂ፣ አስቀድሞ ለተገለጸልህ እውነት ካልታዘዝህ በቀር እግዚአብሔር ለራሱ ሌላ ተጨማሪ እውነት አይገልጽልህም። እንደእነዚያ “ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች እንደተባሉት ማቴ 11:25 “ አትሁን፣ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር ……..ያውቃል” ዩሓ 7:17።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *