ሰሊሆም እና ፍቅር መጽሔት

በዝረወት ኢትዮጵያውያን (ዲያስፖራ) ጸሐፊዎች በውጪ ሃገር የታተሙ መጻሕፍት

ፈጣኑ አሣሄል – በዶ/ር እዮብ ማሞ

ፈጣኑ አሣሄል – በዶ/ር እዮብ ማሞ

ሰሊሆም እና ፍቅር መጽሔት
ዘመኑ ይሁዳ ዳዊትን፣ እስራኤል ደግሞ ሳኦልን የተከተለበት ዘመን ነበር። በሁለቱ ቤቶች ውግያ ንጉሥ ሳኦል ሞቷል። በዚህ ዘመን ነበር አሣሄል የተባለ ፈጣን ሰው ከወንድሞቹ መሃከል በገባኦን ጦር ሜዳ ላይ የተገኘው። የዚህን ... Read more

ከማንበብ ውጭ ሌላ ምርጫ የለንም

ሰሊሆም እና ፍቅር መጽሔት
መስቀል አልባ ክርስትና፣ ክርሰቶስን ጥግ ላይ ያቆመች ቤተክርስቲያን፣ ሰው ሰው ብቻ የሚሸትት አስተምህሮ የነገሠበት ዘመን እኛ እንደምንኖርበት እንደዚህ ያለ ጊዜ ያለ አይመስለኝም፡፡ እኛም ጥቍሩን ጥቍር፣ ነጩንም ነጭ ማለት አቅቶን በምንንገላታበት ... Read more

“እነሆ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው እናገባለን፣ ሥጋቸውንም እንመራለን” (ያዕ. 2፥3)፡፡ ሐዋርያው ይህን ያለው በአስተማሪነት ዐውድ ውስጥ መኾኑን ልብ ይሏል(ቍ. 1-2)፡፡ የአፍ ንግግራችን፣ አስተምህሯችንና ጠባያችን በርግጥ “ልጓም”— የቅዱስ ቃሉና የመንፈስ ቅዱስ ቍጥጥር — ያሻዋል፡፡ ቍጥጥርን ግን ማን ይወዳል? “የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ” በማለትና ቃሉን ያለ መንገዱ በመውሰድ ያለ ቍጥጥር መለቀቅን የምንመርጥ የለንም? መንፈሱ ራስን የመግዛት ቢኾንም (2 ጢሞ. 1፥7)፡፡

በአሽከርካሪው ቸልታም ኾነ በሌላ ምክንያት፣ ከቍጥጥር ውጭ የኾነ ተሽከርካሪ የሚያደርሰውን የንብረትና አሠቃቂ የሕይወት ጥፋት ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ለራሱ የደኅንነት ቀበቶ ያሠረ “ሾፌር” ግን በአመዛኙ ከሚደርስበት የአደጋው ጉዳት ሊያመልጥ ወይም ጉዳቱን ሊቀንስ እንደሚችልም ይነገራል፡፡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሳያደርግና “ሳይታሠር” የሚያሽከረክር ሾፌር ግን ከተያዘ ሊቀጣ ይችላል፡፡ አልያም ምክርና ማስጠንቀቂያ መቀበሉ አይቀርም ብለን እናስባለን፡፡ ዓላማው ጉዳትን በመከላከል የተሳፋሪዎችን ደኅንነት መጠበቅ ነው፡፡

ወንድማችን ሰሎሞን፣ በዚህ መጽሐፉ፣ ለራሳችንና ለምናገለግለው ሕዝብ ደኅንነት ስንል ለመቈጣጠሪያው መንፈሳዊ “ልጓም” ሕይወታችንን እንድንሰጥና ይህንንም ሳናደርግ ቀርተን በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ጉዳት አድርሰን እንዳንገኝ በወንድማዊ ፍቅር ይመክረናል፤ ያስጠነቅቀናል፤ በ“ነቢያዊ” ጩኸቱም ያነቃናል(የምንነቃ ካለን)፡፡ በእውነት ላይ ቆሞ ማስጠንቀቂያ መስጠትም የእውነተኛ ነቢይ ሚና ነው፡፡ የማስጠንቀቅም ዓላማው የሚመለከታቸውን ሁሉ ከአደጋ ማትረፍ ነውና፣ ይህን አዎንታዊ ውጤት እንጠብቃለን፡፡

እንግዲህ፣ መንፈሳዊ መሪዎችና የቃሉ አገልጋዮች እንደ ኾንን የምናስብ ሁላችን፣ ለራሳችን ስተን ብዙዎችን ከማሳት እንድንተርፍ፣ ከጥፋትም እንድንጠበቅ፣ በሰከነ ልብ ይህን መጽሐፍ እናንብብና እንመከር፡፡ “ከባሰውም ፍርድ” እንድንድንና “መልካም፣ አንተ በጎ ታማኝም ባርያ…” ለመባል፣ በሞቱ የዋጀንና ለአገልግሎቱ የጠራን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጸጋው ይርዳን(ያዕ. 2፥1፡፡ ማቴ 25፥21)፡፡

ተስፋዬ ጋቢሶ (መጋቢ)
ከሐዋሣ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን

Our mission is to distribute Christian magazines and books to promote Christian values we find important, and content your whole family can enjoy.

Tsega Books and Magazines

We are in the APPstore – ጸጋ APP

ሰሊሆም እና ፍቅር መጽሔት
ጸጋ – በኢትዮጵያና በሰሜን አሜሪካ የሚታተሙ የአማርኛ ክርስትያን መጽሔቶችን በቀላሉ በኢንተርኔት ወይም በስልክ ላይ ለማንበብ እንዲችሉ የተዘጋጀ ነው:: IPHONE፣IPAD ተጠቃሚዎች የጸጋን APP ከ APP-Store ዳውንሎድ በማድረግ መጽሔቶቹን ማዘዝ ይችላሉ። http://itunes.com/apps/Tsega ... Read more