ባለጸጋ መጽሔት – ከሰሜን አሜሪካ

ባለጸጋ መጽሔት – ከሰሜን አሜሪካ

በምህረቱ ባለጸጋ የሆነው ክቡር አምላካችን ይመስገን::

መንፈሳዊ መልእክቶች ለአማኙ ህብረተሰብ ከሚተላለፉባቸው መንገዶች መሃከል የመጽሔት አገልግሎት ትልቅ ድርሻ አለው:: ሃያ ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ለሚገመተው የኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት አማኞች ያሉትን የመጽሔቶች ቁጥር ስንመለከት ግን አሳሳቢ ነው:: በአንድ ወቅት ብቅ ብለው የነበሩት መጽሔቶች በድንገት ሲጠፉ ብናዝንም እንደ “ባለጸጋ ክርስትያን”፣  “አዳምና ሔዋን”፡ “ሕንጸት” ፡ “ተስፋ”  ያሉት መጽሔቶች ደግሞ በህትመት ዋጋ መናርና በስርጭት ያለውን ችግር ተቁዋቁመው  ከሃገር አልፈው በዓለም ዙርያ ያለውን ዝረወት ኢትዮጵያውያን መድረስ መቻላቸው ለልብ ደስታን ይፈጥራል:: በተለይ ለተደቀነብን ልዩ ወንጌል ምላሽና ምክራቸውን ይዘው የሚወጡት ሕንጸት፡ ዱናቶስ፣ ነገረ ክርስትና፣ ጌሴም፡ ብርሃን እና ተስፋ መጽሔቶች በዓለም ዙርያ ለተበተነው ወገናቸው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደግፈው መቅረባቸው ትልቅ እርምጃ ነው::  ጠፉ ስንባል መብዛታችን በአምላካችን ጸጋ ነው:: ከአልታሰበ ቦታ እግዚአብሄር ሲሰራ አይተው የሚሰሩን ማስነሳትም አምላካችን ታሪኩ ነው :: በምህረቱ ባለጸጋ የሆነው ክቡር አምላካችን ይመስገን::

መልካም ንባብ !

ዋና አዘጋጅ – ኮነ ፍሥሐ

hintsetBaletsegaTesfa2

Now Available online and in Print at www.Tsega.com and at http://free.tsega.com

Tesfa + Hintset + Baletsega = Just $5.00 a month for the three premium Magazines.

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *