ጫካዎቻችን ብዙ ናቸው – ከነገረ ክርስትና መጽሄት የተወሰደ

ጫካዎቻችን ብዙ ናቸው – ከነገረ ክርስትና መጽሄት የተወሰደ

www.Tsega.com: አዎን ማህበራዊ ጫካዎቻችን ብዙ ናቸው፡፡ ጫት ቤቱ መጠጥ ቤቱ፤ ጭፈራ ቤቱ፤ እነዚሀ ሁሉ ማህበረሰቡ ለደስታ ማግኛ ይሁኑኝ ብሎ ያዘጋጃቸው ጫካዎች ናቸው፡፡ ለዚሀ አይነቱ ጥፋት የአንበሳውን ድርሻ እየወሰደ ያለው ጫካ ግን እነሆ ዶ/ር ስዩም አንቶኒዮስ እና ባለቤታቸው ሲሰተር ሳባ ብቻቸውን ሊባል በሚችል መልኩ እየተጋፈጡት ያለው የፓርኖግራፊ ጫካ ነው፡፡ እነዚህ የእግዚአብሄር ሰዎች በአገራችን ዕድል ፈንታ እንዳይኖረው በብርቱ እየታገሉለት ያለው የብዙ ቀላጮች (ግብረሰዶማውያን) ሁነኛው ትምህርት ቤት የሚገኘውም በዚህ የኢንተርኔት ፓርኖግራፊ ጫካ ውሰጥ ነው፡ እነርሱስ ሰነባብተዋል፡፡ ተገናቸው ያደረጉት እግዚአብሄርን በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ እንድጽፍ ምክንያት የሆነችኝ እህት ጨምሮ በጩህታቸው የሚድኑ ብዙ ወላጆች እንደሚኖሩም ተስፋ አለኝ፡፡

አዎን .. ከዚሀ ጫካ የሚወጣውና ሰው ከአውሬነቱ የሚፈታው እንዴት ባለ ዘዴ ነው? ለሚለው ጥያቄ በዋናነት መልሱ የሚገኘው በእግዚአብሄር መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ገና ሰውን የራሱ ግማሽ መንገድ ለመሄድ የሚያስችለውን አንድ የመፍትሄ አቅጣጫ ጠቅሼ ነገሬን ልቋጭ። ምክረ ሀሳቡ የስነ መለኮት መምህርና ሰባኪው ወንደም ማሙሽ ፈንታ (በአሁኑ ጊዜ ዶ/ር) ሲሆን ቀደም ብዬ በጠቀስኩትና ከጥቂት አመታት በፊት “የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች ተማሪዎች ህብረት›› /ኢቫሱ/ በኮሌጅና ዪኒቨርሲቲ ለሚማሩ ተማሪዎች አዘጋጅቶት በነበረው የፓናል ውይይት ላይ ፖርኖግራፊን አስመልክቶ ላቀረቡት የጥናት ጽሁፍ መደምደሚያ ነው፡፡ የኔም ርእሰ ጉዳይ መቋጫ እንዲሆን መርጬዋለሁ፡፡

ማሙሻ በንግግራቸው መግቢያ ላይ “ፖርኖግራፌ›› ማንኛውም ወሲብ ቀስቃሽ የሆነ ትእይንት ማለት እንደሆነ ሲገልጹ የትም ስንሄድ ተመልከቱን እና አንብቡን እያሉ እረፍት የሚነሱን በየትኛውም ቴክኖሎጂ  ውስጥ በቀላሉ የምናገኛቸው አእምሮና ስጋን በወሲብ ሀሳብ ለማጥመድ ሆን ተብለው የሚሰሩ ስራዎች ሰለመሆናቸው ሰፊ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ “ፓርኖግራፊ ማለት እግዚብሔር በቃሉ እንዳናደርገውና እንዳናስበው የፈለገውን ነገር እንድናደርገውና እንድናስበው የሚገፋፋ ትክክለኛ ላልሀነ የወሲብ ምኞትና ድርጊት ሰውነታችንን የሚያመቻች ወይም የሚያነሳሳ አለማዊ ተግባር ነው፡፡›› ያሉት ማሙሻ ፓርኖግራፌ ለተጠቃሚው ከሰጠው ግዚያዊ ደስታ በላይ ይዞት ሰለሚመጣው ጣጣም እንዲሁ ብለዋል፡-

አንደኛ፡ ሀጥያት በመሆኑ ሀጥያታዊ ችግሮችን በሙሉ ያመጣል፡፡ ሐጢያት የሚያስከትለውን ጠንቅ ሁሉ ይዞ ይመጣል፡፡ ጌታችን እየሱስ አንድ ሰው ወደ ሴት ተመልክቶ በልቡ ከተመኛት ያ ሰው አመንዝሯል እንዳለ ፓርኖግራፌ በሀሳብ ለሚሰሩ የዝሙት ሃጥያቶች አቀጣጣይ በመሆን ህሊናን የሳድፋል ፡፡

ሁለተኛ፡-  ተጠቃሚውን ሱሰኛ በማድረግ ሊወጣው ከማይችል የምኞት ዓለም ውስጥ ያስገባዋል፡፡ የፓርኖግራፊ አንዱ ቅንብር በሰውየው ውስጥ የማይሞላ የእርካታ ተስፋን በመቀለብ ከአንዱ ትእይንት ወደሌላው እንዲሻገር የሚያስገድድ በመሆኑ ስሜትና ቀልብን አጥምዶ የመያዝ ጉልበት አለው፡፡

ሶስተኛ፡- የፓርኖግራፊ ሰለባነት በግለሰቡ ስሜት ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን ወደ ማህብረሰቡም የመሻገር አቅም አለው፡፤ ፓርኖግራፊ ቦንብ በሰውየው ውስጥ ተጠምዶ በሰውየው ውስጥ የሚፈነዳ ነገር አይደለም፡፡ ሰውየው ቅስቀሳው ሲበረታበት ስሜቱን ለማርካት ወደ አደባባይ መውጣቱ የማይቀር ስለሆነ ከህጻናት ጀምሮ በየትኛውም እድሜ ያለን ሰው ለመድፈር የሚያስቃጣ ሃይል አለው፡፡

አራተኛ፡- ፓርኖግራፊ የሰውን ዋጋ ያሳንሳል፡፡ ሰውን አሳንሶ …አሳንሶ..አሳንሶ ለወሲብ ብቻ የተፈጠረ ያደርገዋል፡፡ ሰው አካሉን ብቻ እንጂ ነፍስና መንፈስ ያለው ረቂቅ ፍጡር መሆኑን ያዘነጋል፡፡

አምሰተኛ፡ ጊዜንና ሃብትን ጋጥ አድርጐ ይበላል፡፡ ፓርኖግራፌ ሰውን ከዓለማው አውርዶ በቂጡ ቁጭ የሚያደርግና የሚያነሆልል ነገር በውስጡ ይዟል፡፡

ወንድም ማሙሻ ይህንን ከተናገሩ በኃላ “እንግዲያውስ እንደ ክርስቲያን ከኛ የሚጠበቀው ምንድነው?›› ለሚሉ ወጣቶች የለገሱት ቀጣዩ ምክርም የሚከተለውን ይመስላል፡፡

መፍትሔ1- መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚል ከዝሙት ሽሹ በዝሙት ፊት ጀግና ስለሌለ ዳር ዳር ማለት አያሻም በዚህ ጉዳይ ::

ነገረ ክርስትና መጽሔትን በአዲስ አበባ የክርስትያን መጽሄት መደብሮች ያገኛሉ እንዲሁም በውጪ ሃገር ለምትኖሩ ደግሞ  ከ www.TSEGA.COM  ማዘዝና ማንበብ ትችላላችሁ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *