ከበደ ሚካኤል

ከበደ ሚካኤል

ከበደ ሚካኤል የሰዎች ስነ ምግባር ላይ የማተኮርና ምክር አዘል መልእክቶችን የማስተላለፍ ዝንባሌአቸው በአብዛኛው ስራቸው ላይ ይንጸባረቃል። በፈረንሳይ ሚሽን ትምህርታቸውን መከታተላቸው ይህን ቅን የስነምግባር አመለካከት ፈጥሮባቸዋል። ዘመናዊት ኢትዮጵያን ለማደርጀት በተደረገው ትግል በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ እኒህ ፈላስፋ፥ ባለቅኔ፥ ጸሐፌ-ተውኔት፥ ደራሲና አንጋፋ ጋዜጠኛ ፥ ‘የቀለም ሰው’ በሀገራችን የመጀመሪያ የነበረውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት ሜዳልያን በቀዳሚነት የተቀበሉ ሲሆን፣ አዲስ ትውልድ ላፈራ ስብእናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. በሥነ ጽሑፍ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሸልሟቸዋል። በተረፈም ከፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሶቭየት ህብረትና ሜክሲኮ ሽልማትን ተቀብለዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *